Analysis of Costs of Production and Profitability for Irrigated Cotton under Smallholder Production Systems; the Case of Middle Awash Valley

Autor: Belay, Getinet, Yami, Mesay, Bekele, Adam
Jazyk: angličtina
Rok vydání: 2020
Zdroj: Ethiopian Journal of Agricultural Sciences; Vol 30, No 1 (2020): Ethiopian Journal of Agricultural Sciences; 1-16
ISSN: 0257-2605
2415-2382
Popis: አህፅሮትቀጣይነት ያለዉ የግብዓት ዋጋ ጭማሪና የጥጥ ምርት ዋጋ መዋዠቅ በአነስተኛ አምራቾች ዘንድ የጥጥ ምርትን ትርፋማነትና ዘለቄታዊነት ጥያቄ ዉስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል፡፡ ይህ ጥናት በአነስተኛ አምራቾች ዘንድ በመስኖ ጥጥን ለማምረት የሚከናወኑ ተግባራትን ከትርፍ አንጻር ለመገምገም በመካከለኛዉ አዋሽ አሚባራ ወረዳ የተከናወነ ነበር፡፡ ጥናቱ 30 የሚሆኑ አነስተኛ የመስኖ ጥጥ አምራቾችን በአላማዊ ናሙና በመምረጥ የተካሄደ ሲሆን የመስኖ ጥጥ ምርት ወጪና ትርፍን ለመለካት የሚያስችሉ ገላጭና የበጀት ቴክኒኮችን ለትንተና ተጠቅሟል፡፡ በተመሳሳይ ትርፍም ኪሳራም የሌለበትን የዋጋና የምርት መጠን እንዲሁም ሊያጋጥሙ የሚችሉ ለዉጦችንና ስጋቶችን ግምት ዉስጥ በማስገባት ትንተና ተካሂዷል፡፡ ዉጤቱም እንደሚያሳየዉ የመስኖ ጥጥን ለማምረት ከሚወጡት ወጪዎች መካከል የሰዉ ጉልበት፤የኬሚካልና የማሽነሪ ወጪዎች ዋናዎቹ ሲሆኑ የባጀት ትንተናዉ ዉጤትም ጥጥ ማምረት በአነስተኛ አምራቾች ደረጃ ትርፋማ እንደሆነ አመላክቷል፡፡ በአነስተኛ አምራቾች ዘንድ ጥጥን በመስኖ ለማምረት የሚያስፈልገዉ የስራ ማስኬጃ ወጪ 20,572.17 ብር በሄክታር የነበረ ሲሆን በተመሳሳይ የተገኘዉ ትርፍ በሄክታር 10,294.23 ብር ነበር፡፡ በተጨማሪም የጥቅም-ወጪ ንጽጽር 1.49 ነበር፡፡ ትርፍ-ኪሳራ አልባ ዋጋና የምርት መጠን ደግሞ 8.35 ብር በ ኪ.ግ እና 1641.83 ኪ.ግ በሄክታር በቅድመ-ተከተል ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ጥናቱ ከመስኖ ጥጥ የሚገኝ ትርፍ ከስራ ማስኬጃ ወጪዎች ይልቅ በምርትና በምርት ዋጋ መቀያየር የበለጠ የሚጠቃ መሆኑን አሳይቷል፡፡ ስለሆነም የጥጥን ትርፋማነትና ምርታማነት ይበልጥ ለማስቀጠል የምርት ዋጋን ማረጋጋትና ምርትን ሊያሳድጉ የሚያስችሉ ግብዓቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ እንደሚገባ ጥናቱ ያመለከተ ሲሆን የተሳለጠ የግብዓትና ምርት ግብይት ይኖር ዘንድ ማህበራትን ማደራጀት ያስፈልጋል፡፡ AbstractThe continuous increase of input costs and volatility of output prices have made the profitability and sustainability of smallholder cotton production in question. This study was carried out to examine the profitability of irrigated cotton production at Amibara district in the Middle Awash Valley under smallholder producers. 30 producers were purposively selected from the villages considered based on the predominance of irrigated cotton production. Primary data were collected for this study using well-structured questionnaires. Data were analyzed using descriptive statistics and budgetary technique analysis. Likewise, break-even and sensitivity analyses were introduced to determine the break-even price and yield and to account to any changes and risks envisaged. The break-up of production cost structure showed that operational (both manual and machinery) expenses were the prominent components of all variable costs. The principal findings of the enterprise budget analysis was that smallholder irrigated cotton production was a profitable enterprise with a gross margin of 10,294.23 Birr per hectare and a total expenditure of 20,572.17 Birr per hectare. Moreover, the benefit cost ratio of 1.49 was obtained. The break-even price and break-even yield at which the producers are at no loss no profit were 8.35 Birr per kg and 1641.83 kg per hectare. Returns from irrigated cotton were highly sensitive to fluctuations of price and yield than total variable cost. Thus, efforts should be made to improve productivity through provision of appropriate agricultural inputs at the lowest possible cost and reduce price volatility by promoting primary cooperatives at district level working on input output marketing.
Databáze: OpenAIRE